”ህንግጫ”ማህበራዊ መስተጋብር የሚያጠናክር፣የኮንታ ብሔር ማንነት ምልክትና የአከባቢው የማይነጥፍ የእንግዳ ተቀባይ መገለጫ ነዉ፦አቶ አልማዉ ዘዉዴ

Spread the love

”ህንግጫ”ማህበራዊ መስተጋብር የሚያጠናክር፣የኮንታ ብሔር ማንነት ምልክትና የአከባቢው የማይነጥፍ የእንግዳ ተቀባይ መገለጫ ነዉ፦አቶ አልማዉ ዘዉዴ

የኮንታ ብሔር የዘመን መለወጫ “ህንግጫ”በዓል በአመያ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ትውፊቶችና ክዋኔዎች የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የኮንታ ወዳጆች በተገኙበት ተከብሯል።

በበዓሉ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማዉ ዘዉዴ፤ የምስጋና፣ ብርሃን፣ ጥጋብ ፣ሰላም፣ አንድነት፣ የአብሮነት እና የፍቅር መገለጫ ለሆነዉ ለኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ ህንግጫ በዓል እንኳን አደረሳችሁ/ አደረሰን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

”ህንግጫ’ ማህበራዊ መስተጋብር የሚያጠናክር፣የኮንታ ማንነት ምልክትና የአንድነት ቀለም እንዲሁም የአከባቢው የማይነጥፍ የእንግዳ ተቀባይ መገለጫ ነው ሲሉም አቶ አልማው ዘዉዴ ጠቅሰዋል።

ጠንካራ ማህበረሰብና ሀገር ለመገንባት እንደ “ህንግጫ” ያሉ በዓላት የጎላ ሚና እንዳላቸው የተናገሩት አቶ አልማው ኮንታ ዞንን ከባህላዊ እሴቶች ባሻገር ካለው እምቅ የቱሪዝም ሀብት ጋር በማስተሳሰር ማስተዋወቅና ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ህንግጫ በዓል በውስጡ የያዛቸዉ በርካታ የብሔረሰቡ ቱባ ባህሎች ፓርቲ በሀገር ለሚገነባው ብልጽግና ጉዞ ጠንካራ መሠረት የሚጥል በመሆኑ ማልማት፣በመጠበቅና በመንከባከብ ለቀጣዩ ትውልድ ማሻገር እንደሚጠበቅ ነዉ አቶ አልማዉ ዘዉዴ የገለጹት።

የክልሉ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ በበኩላቸዉ ህንግጫ በዓል በድሮ አያቶቻችን ተጠብቆ ከዘመን ወደ ዘመን ባህላዊ ይዘቱን ሳይለቅና ሳይደበዝዝ ሲከበር ለአሁኑ ትውልድ የተሸጋገረ የብሔሩ ዘመን መለወጫ በዓል ነው።

ህንግጫን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ የብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላትና ሌሎች ባህላዊ ቱባ ባህሎች የሀገር የማይዳሰስ ቅርስ ሆነዉ እንዲያገለግልና ለሀገር ልማት ግንባታ እንዲዉሉ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉም አቶ ፋንታሁን ብለቴ ገልጸዋል።

የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ህንግጫ” የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል በአደባባይ ሲከበር በሀገሪቱ ከሚከበረው ጳጉሜ 3 የ”እምርታ ቀን” ጋር መከበሩና ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት መንግስት በገባው ቃል መሠረት አባይ ግድብን ጨምሮ ታላላቅ ድሎችን ባስመዘገበት ወቅት መሆኑ ልዩ እንደሚደረግ አስረድተዋል።

“ህንግጫ” በኮንታ ብሔረሰብ ልዩ ስፍራ የሚሰጥ በመሆኑና ለሰላም፣ ለፍቅርና ለአብሮነት ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን አንስተው ይህንንም ማጠናከር ከሁሉም አካላት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ በርካታ ብሔር፣ብሔርሰቦችና ህዝቦች መገኛ፣በርካታ የተፈጽሮ ጸጋዎች፣የህዝቦች የጋራ መከባበርና መተባበር እንዲሁም ህብረብሔራዊነት የሚንጸባረቅበት በመሆኑ በዓለም ደረጃ ጎልተን እንዲንታይ አስችሎናል ሲሉም ዋና አስተዳዳሪዉ ጠቅሰዋል።

የኮንታ ቀደምት አባቶች ጠብቀዉና ተንከባክበው ለቀጣዩ ትውልድ ካስተላለፉት በርካታ ባህላዊ፣ታሪካዊ፣ ትውፊቶችና እሴቶች መካከል የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ ህንግጫ አንዱ እንደሆነም ያብራሩት የኮንታ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ

ኃላፊ አቶ አበበ ደምሴ ናቸዉ።

ህንግጫ የጎዶሎዉ ሙላት፣ያለውን ለሌለው የሚያካፍልበት ፣እርቀ-ሰላም የሚወርድበት፣ የማህበራዊ ትስስር የሚያጠናክር ነዉ ያሉት የመማሪያዉ ኃላፊ በኮንታ ዞን የሚገኙ በርካታ ባህላዊ ትዉፍቶች፣የቱሪስት መዳረሻዎች እና የቱሪዝም አለኝታ ጸጋዎችን መንከባከብ፣መጠበቅና ማልማት ከሁሉም የሚጠበቅ ነዉም ብለዋል።

በፍቅር ከበደ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *