




በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ጨምሮ፣ የሀገራት አምባሳደሮችና ሌሎችም ሚኒስትሮች ተግኝተዋል።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፤ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ግብይት የኢትዮጵያ ወጪ ንግድ ከማሳለጥ ረገድ ሚናው የጎላ ነው።
ከዚህ ባለፈም የኢትዮጵያን የንግድ ዘርፍ መስፈንጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል፡፡
በተለይ በእቃዎች ዋጋ ተመን (ታሪፍ) ላይ ስምምነት ተደርሶ፣ ዛሬ የመጀመሪያውን ጭነት በአየርና በየብስ መላክ መጀመሩን አብስረዋል።
ግብይቱ መጀመሩን አስመልክቶ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና በየብስ ትራንስፖርት አማካይነት ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ አፍሪካ ተልከዋል።
