
የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መሰለ ከበደ ምክር ቤቱ 3ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በቴፒ ከተማ እንደሚያካሂድ ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ጉባኤ እንደሚያካሂድ የገለጹት አቶ መሰለ በሕገ መንግሥቱ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አስቸኳይ ጉባኤ ስያስፈልግ እንደሚያደርግ አስረድተዋል።
አቶ መሰለ አክለውም በክልሉ የሚኖሩ ብሔረሰቦች አንድነትና ትስስራቸው እንዲጠናከርና እንዲጋመድ በርካታ ሥራዎች ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትና ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለመፍጠር፣ብዝኃነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የሀብት ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል።
በዕለቱ የክልሉ መንግሥት ተወካዮች፣ የምክር ቤቱ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉባኤው ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
