ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ሊያካሂድ ነው

Spread the love

​የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መሰለ ከበደ ምክር ቤቱ 3ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በቴፒ ከተማ እንደሚያካሂድ ገልጸዋል።

​ምክር ቤቱ በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ጉባኤ እንደሚያካሂድ የገለጹት አቶ መሰለ በሕገ መንግሥቱ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አስቸኳይ ጉባኤ ስያስፈልግ እንደሚያደርግ አስረድተዋል።

​አቶ መሰለ አክለውም በክልሉ የሚኖሩ ብሔረሰቦች አንድነትና ትስስራቸው እንዲጠናከርና እንዲጋመድ በርካታ ሥራዎች ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትና ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለመፍጠር፣ብዝኃነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የሀብት ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል።

​በዕለቱ የክልሉ መንግሥት ተወካዮች፣ የምክር ቤቱ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉባኤው ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *