


አየር ኃይል የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ ለመፈፀም በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል አሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ፡፡
የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር ኦፕሬሽን በግዳጅ አፈጻጸም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ክፍሎች እውቅና ሰጥቷል፡፡
ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ በዚህ ወቅት÷ተቋሙ የሚሰጠውን ተልዕኮ እና ግዳጅ ለመፈፀም በከፍተኛ የዝግጁነት አቅም ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል ።
አየር ኃይል በአጭር ጊዜ ባከናወናቸው የለውጥ ሥራዎች አስደናቂ ስኬቶችን አስመዝግቧል ያሉት ዋና አዛዡ ÷ ይህም የአመራሩና የአባላቱ የጋራ ሥራ ውጤት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
አየር ኃይል ም/አዛዥ ለአየር ኦፕሬሽን ብ/ጄ ተስፋዬ ለገሰ በበኩላቸው÷ ክፍሉ የኢትዮጵያን የአየር ክልል በንቃት በመጠበቅ የተቋሙን የውጊያ ዝግጁነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ግዳጃቸውን በብቃት ለተወጡ ክፍሎች የእውቅናና የምስጋና ሰርተፍኬት መሰጠቱንም የመከላከያ ሠራዊት ኦንላይን ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ሌ/ኮ ውብሸት ቸኮል ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል።
