የመደመር መንግሥት

Spread the love

የመደመር መንግስት የነገን የተሻለ ለማድረግ የትናንት፣ የዛሬን የነገ ተደራራቢ ኃላፊነቶቻችንን በአስቸኳይ እንድንወጣ ያደርጋል። እንዲሁም ተለዋዋጭ በሆነዉ የዓለም ሁኔታ ውስጥ፣ ጥንካሬያችንን ለማረጋገጥና ከግባችን ለመድረስ እንድንፈጥን ያስችላል።

የመደመር መንግስት ፍጥነትና መስረት ያደረገ ዕሳቤ ነዉ። የዚህ መጽሐፍም ዋነኛ ጭብጥ ይህንን የፍጥነትና የፈጠራ ፍኖት ማብራራት ነዉ። ሀገራችን ካለችበት የግርጌ ደረጃ ተሰፈንጥራ ወደ ራስጌ መዉጣት የምትችልበትን ሐሳብ የሚያቀብል ነዉ።

በዋናነት የተረከብነዉን የተከማቸ ችግር በፈጠራና በፍጥነት ለመፍታት እንድንችል የሚያደርግ የተሻለ ስርዓት ስለመገንባት ያወሳል። ሀገራችንን ካለችበት ሁኔታ ወደ ብልጽግና ማማ ጫፍ ማሻገር፣ በዘመን አጋጣሚ የዚህ ትዉልድ ኃላፊነት ሆኗል። ኃላፊነታችንን በሚገባ በመወጣት፣ ለልጆቻችን የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ በጋር እንነሳ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *