




መድረኮቹ በሁሉም ዘርፎች የተመዘገበዉን ለዉጥ በማስቀጠል የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቅነት በመፍታት የህዝቡን ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፍ ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነው።
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ውይይቱን የመሩት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ መጠነ ሰፊ ተግባር መከናወኑን ገልጾ በዚህም ለህዝብ ድምፅ ትኩረት በመስጠት ማዘጋጃ ቤት ላይ ያደረገው የሪፎርም ስራና 13 ሰራተኞችን ወደ ሌላ መስሪያ ቤት እንዲመደቡ ማድረጉ ነው ብለዋል።
የማዘጋጃ ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን በዲጂታል እየተደረገ ያለው ስራ እና እንዲሁም ነዋሪዎች የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲያገኙ የሰራ ተግባር ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል።
የሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ውይይት ላይ የተገኙት የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አጥናፉ ኃይሌ የለውጡ መንግስት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በየወቅቱ መንግስት ህዝባዊ ውይይት እያደረገ መቆየቱን ጠቁመው በዛሬው ውይይት ከዚህ በፊት ምላሽ ያላገኙና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች በግልጽ አንስተን የሚንመክርበት መድረክ ነው ብለዋል።
በዳካ ከተማ አስተዳደር ውይይት ላይ የተገኙት የካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ መሸሻ እንደገለፁት የኢትዮጵያን ማንሰራራት እዉን ለማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ ያስፈልጋል ብለዋል::
በከተማው የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በበለጠ ሁኔታ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሙሉጌታ በነዋሪዎች ዘንድ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ካሉ በመቅረፍ የአካባቢዉን ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡
በመድረኮቹ ላይ የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የየከተማ ከንቲባዎች እና ሌሎች አመራሮች እንድሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ነዋሪዎች እየተሳተፉ መሆኑን መረጃዎችን መሆኑን የየከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
በአሻግሬ ገ/ወልድ
