በኮንታ ዞን 18 አመራሮች ከኃላፊነት ተነሱ

Spread the love

በኮንታ ዞን አመራር ውጤታማነትን፣ ስነ ምግባርንና ዝግጁነትን መሠረት ባደረገ ጥብቅ ምዘና፣ በዞኑ የሚገኙ 71 አመራሮችን ከዞን እስከታችኛዉ መዋቅር የማንሳት፣ የማሸጋሸግና አዲስ ምደባ ማከናወኑን የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት፡

18 አመራሮች ከኃላፊነት ተነስተዋል።

25 አመራሮች ሽግሽግ ተደርጓል።

28 አዳዲስ አመራሮች ወደ ኃላፊነት መጥተዋል።

ይህ እርምጃ በተለይ ወጣቶችንና ሴቶችን ያገናዘበ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ አዲሶቹ ኃላፊዎች የህዝብን አደራ በብቃት እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸዉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *