




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ SNV HORT LIFE 3 ፕሮግራም ጋር በመተባበር የአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት ተቋማዊ ማድረጊያ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በክልሉ (SNV HORT LIFE 3) ፕሮጀክት በ18 ወረዳዎች የሚሰራ ሲሆን ከዚህም በ11 ወረዳዎች በቀጥታ እና በቀሪ 7 ወረዳዎች በቢሮ ሆነ በተለያዩ ፕሮግራሞች ድጋፍ በአርሶ አደሮች መስክ ትምህርት ቤት ላይ እንደሚሰራም ገልጸዋል ።
ፕሮጀክቱ በ18 ወረዳዎች ባሉት ወደ 228 ገዳማ በሚሆኑ አርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤቶች ላይ ከ9 መቶ በላይ የሚሆኑ ሠርቶ ማሳያዎችን በማዘጋጀት የአርሶ አደሩ ማሳ የግብርና ቴክኖሎጂ ሥርፀት ማዕከል እንዲሆን በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል።
በክልሉ በፕሮጀክቱ በተሰሩ ሥራዎች ጥሩ የተመዘገቡ ለውጦች እንዳሉትም ያነሱት አቶ ማስረሻ በላቸው ተግባሩን ቀጣይ ተቋማዊ የማድረግ ሥራዎች እየተከናወነ ይገኛልም ብለዋል።
በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች የሆርቲካልቸር ሰብል፣ፍራፍሬ እና በአትክልት የሚከናወኑ ተግባራት እና በዚህም በተመዘገቡ ውጤቶች የፕሮጀክቱ አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነም ጠቅሰዋል አቶ ማስረሻ በላቸው።
በፕሮጀክቱ በታቀፉ ወረዳዎች ሆነ ከዛ ውጪ በሆኑ አከባቢዎች ተግባሩ እንዲሰፋ እስካሁን ከተከናወኑ ሥራዎች ልምድ በመውሰድ ቀጣይ ሥራዎችን ለማስፋፋት መድረኩ ታስቦ ተዘጋጅቷል ብለዋል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ።
በመድረኩ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የግብርና ቢሮ ኃላፊዎች፣የዞን አስተዳዳሪዎች፣የዞን ግብርና፣አከባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በፍቅር ከበደ
