
በዳውሮ ዞን በቅርቡ በተደረገ ጥብቅ ግምገማ ላይ ተመስርቶ በተወሰደው እርምጃ ከዞን አስከታችኛዉ መዋቅር 59 አመራሮች ሙሉ በሙሉ ከኃላፊነታቸው የተነሱ ሲሆን፣ ሌሎች 55 አመራሮች ደግሞ የኃላፊነት ሽግሽግ ተደርጓል።
የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኢዮብ ቶማስ እንደገለጹት፣ ይህ እርምጃ የተወሰደው ያለፈውን ዓመት አፈጻጸም ከመዘነ በኋላ መጪውን ተልዕኮ በብቃትና በስነ ምግባር ሊያስፈጽም የሚችል ጠንካራ አመራር ለመፍጠር ነው።
በዚህም መሰረት 35 አዳዲስ አመራሮች ወደ ኃላፊነት የመጡ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 149 አመራሮችን ያካተተ ከኃላፊነት የማንሳት፣ የማሸጋሸግና አዲስ ምደባ ተከናውኗል ማለታቸዉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
