



የውይይቱ ዓላማ በከተማ አስተዳደሩ በሁለቱም ዘርፎች በመንግስትና በፓርቲ የተከናወኑ ተግባራት ለነዋሪዎች ማሳወቅና ጠንካራና ውስንነቶችን በመለዬት በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎችን በመለዬት በቀጣይ የሚሰሩ የልማት ስራዎችን ለማጠናከር መሆኑ ተገልጿል።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ እንደተናገሩት ለአንድ ከተማ ዘላቂነት ያለው ልማትና ዕድገት እንዲመዘገብ ለማድረግ የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።
በዚህም በከተማዋ በሚሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ማህበረሰቡን በቅርበት በመደገፍና በማሳተፍ ተጨባጭ ውጤቶች እየታዩ መምጣቱን ተናግረዋል።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ጊስካር በበኩላቸው የከተማችን ህዝብ በሁሉም መስክ በከተማችን እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ላይ እያሳዬ ያለው ድጋፍ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል ብለዋል።
በከተማችን የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን በእጅጉ እያደገ ነው ያሉት ዋና የመንግስት ተጠሪው የነዋሪው ህዝብ የመልማት ፍላጎትም በእጅጉ እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል።
ከከተማው ዕድገት ጋር ተያይዞ ሊመጡ የሚችሉ የማህበረሰብ እሴቶችን የሚሸረሽሩ ችግሮችን ለማረም የሁሉም ማህበረሰብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ ወይዘሮ አሰገደች ፍቅሩ በከተማዋ እየተሰሩ ባሉት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙሪያ የውይይት መነሻ ሰነድ እያቀረቡ ይገኛል ሲል የዘገበው የሚዛን አማን ከተማ ኮምኒኬሽን ነው።
