



በየደረጃው ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ችግር ፈቺ ምላሽ ከመስጠት አንጻር የሚስተዋለውን ክፍተት ለማረም የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጠባቸው ፓርቲው አመላክቷል ።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ልዩ አማካሪ አቶ አለማየሁ አይበራ የመንግስትን እና የፓርቲ ስራዎች የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሥራ ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመላከቱት ተልዕኮውን በብቃት መምራት የሚችል የፓለቲካ ስርዓት ለመገንባት እየተሰራ ነው ።
ተልዕኮውን በብቃት የሚወጣ አመራር በየደረጃው በመመደብ ውጤታማነትን ለማሳደግ እየተደረጉ ካሉ ጥረቶች የግምገማና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ጠቅሰዋል።
በሩብ ዓመቱ የተደረገው ግምገማና የማጥራት ሥራ ለቀጣይ ተልዕኮዎች መሰረት የሚጥል መሆኑን ነው ያነሱት።
ከህዝቡ ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ችግር ፈቺ ምላሽ ከመስጠት አንፃር ክፍተት መኖሩ በግምገማው መረጋገጡን በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል ።
መልካም ልምዶችን በመቀመር ከማስፋት ባሻገር ጉድለቶችን ለማረም የሚያስችሉ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውንም የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ልዩ አማካሪ አቶ አለማየሁ አይበራ መግለጻቸዉን ካፋ ቴቪ ዘግቧል።
በቅርቡ የተካሄደው የአመራር ሽግሽግ በየዘርፉ የተጀመሩ ተግባራትን ከዳር ለማድረስ እንደሚያግዝ በመድረኩ ተጠቁሟል ።
