በክልሉ ኢንቨስትመንትን በማስፋት እና የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በማሻሻል ገቢ ለማሳደግ በተሰጠው ትኩረት አውንታዊ ውጤት ተመዝግቧል።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈጻጸም በክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ እየቀረበ ይገኛል።

በበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት እና የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በማሻሻል የክልሉን ገቢ ለማሳደግ በተሰጠው ትኩረት አመርቂ ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰች ቶማስ የገለጹ።

በ2018 በጀት ዓመት፣ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 21 የተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ፍቃድ ማግኘታቸውን የገለጹት ወ/ሮ ወሰነች ይህም ከ3 መቶ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

በሩብ ዓመቱ የኢንቨስትመንት ውሳኔ ላገኙ ፕሮጀክቶች የሚውል ከ1ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መተላለፉም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ላይ የተሰማሩ የንግድ ተቋማትን በመለየት ህጋዊና አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን መስጠት መቻሉንም ነው ወ/ሮ ወሰነች በሪፖርቱ ያመላከቱት።

የታክሲ ውሳኔ ቅረታ አቀራረብን በማሻሻል ግብር ከፋዩ በተቋሙ ላይ እምነት እንዲኖረው ማድረግ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን የገቢ መሠረቶችን በማስፋት በሩብ ዓመቱ 3ቢሊዮን 700 ሚሊዮን ገብ መሰብሰብ መቻሉ የተገለፀ ሲሆን ይህም የዕቅዱ 88 ከመቶ መኾኑ ተመላክቷል።

የታክሲ አሰባሰብ ፍትሀዊነት በማረጋገጥ ታክስ ካልኾኑ ምንጮች የሚሰበሰበውን ገቢ በቀጣይ ማሳደግ እንደሚገባ ኃላፊዋ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።

ለማዕድን ሀብት ልማት በተሰጠው ትኩረት በበጀት ዓመቱ አመርቂ ውጤት መመዝገቡ የገለጹት ወ/ሮ ወሰነች በዚህም 53 አዳዲስና ነባር የማዕድን ፍቃድ መታደሱን ገልጸዋል።

ወርሀዊ የወርቅ አቅርቦት 149 ኪሎግራም መድረሱን የገለጹት ኃላፊዋ፣ 82ሺህ 410 ቶን የድንጋይ ከሰል ምርት መውጣቱንና ከዚህም ከ44 ሚሊዮን ብር በላይ የሮያሊቲ ክፍያ መገኘቱን ተናግረዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *