የዜጎችን ሁለንተናዊ ኑሮ ለማሻሻል በተከናወኑ የማኅበራዊ ዘርፍ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡ ተገለጸ።

Spread the love

በበጀት ዓመቱ አንደኛው ሩብ ዓመት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የዜጎችን ሁለንተናዊ ኑሮ ለማሻሻል በተከናወኑ የማኅበራዊ ዘርፍ ተግባራት አበረታች ለውጥ መመዝቡ ተገልጿል።

ይህ የተገለጸው የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ፤ የክልሉን የ2018 የአንደኛው ሩብ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው።

በጤናው ዘርፍ በበጀት ዓመቱ፥ የማዐጤመ አግልግሎት ለማሻሻል ከ139 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ለ121 ጤና ጣቢያዎችና 11 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ማስተላለፍ መቻሉን ወ/ሮ ወሰነች ገልጸዋል።

ለጤና እና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ምላሽና ህክምና አግልግሎት 14 ሚሊዮን ብር የሚገመት መድኃኒትና የህክምና አግልግሎት አቅርቦት ማሳለጥ መቻሉም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በክልሉ የወባ ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ትኩረት ተደርገው ተሰጥተው እየተከናወነ እንደሆነና በዚህም የወባ የመገኘት ምጣኔ 54 ከመቶ የደረሰ ሲሆን ተገቢውን ህክምናና መድኃኒት ማቅረብ መቻሉ ተገልጿል።

በክልሉ የትምህርት አግባብነት፣ ጥራት፣ ፍትሀዊነት እንዲሁም ተደራሽነት ለማሻሻል በተሰጠው ትኩረት ውጤት መመዝቡን የገለጹት ወ/ሮ ወሰነች፥ የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል ቀጣይነት ያለው ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በ2017 ክልላዊ ፈተና ከወሰዱት መካከል 20ሺህ 744 ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ማለፋቸው የተገለጸ ሲሆን ይህም የእቅዱ 57 ከመቶ መኾኑ ተገልጿል።

በበጀት ዓመቱ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል 650 ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ይህም ከአምናው መሳሳይ የትምህርት ወቅት ጋር ስነጻጸር መጠነኛ መሻሻል ያሳየ ቢሆንም ከሀገራዊ ውጤት አኳያ ስታይ አነስተኛ በመኾኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል።

የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል የተጀመረው ቀጣይነት ያለው ተግባር መጠናከር እንዳለበት በሪፖርቱ የተመላከተ ሲሆን የትምህርት ቤት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይተው መፍታት እንደሚገባም ተገልጿል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *