ባለፉት ስድስት ወራት ያገኘነዉን ዉጤት አስጠብቀን በቀጣይ የተሻለ ለማስመዝገብ እንሰራለን:።ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በሰጡት ማጠቃለያ ምላሽ የምክርቤት አባላት ያነሱት ጥያቄዎች ከአዲጊ ፍላጎት የመነጨ መሆኑን በመግለጽ ተገቢነት ያለው ነው ብለዋል።

ከቀድሞ ደቡብ ክልል ይዘናቸው የመጡ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ አለመጠናቀቃቸው ክልሉ ይዞት የመጣው የ5 ቢሊየን ብር ዕዳ የመመለስ ሁኔታ መኖሩን አብራርተዋል ።

ከ2014 ጀምሮ እስከ 2015 ከነበረው 5 ቢሊዮን ዕዳ ውስጥ 3.5ቢሊዮን ብር መመለስ መቻሉን ተናግረዋል ።

በክልሉ የልማት ስራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ።

በዚህም የአርሶአደሩን ኢኮኖሚ ማሳደግ መቻሉንና ገና በርካታ ስራዎችን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን አብራርተዋል ።

የክልሉ የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በራስ አቅም የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ገልጸዋል።

በክልሉ ያልተመለሱ የአፈር ማዳበሪያ ዕዳዎች መኖራቸዉን ገልጸዉ የታችኛው መዋቅር ያልተመለሱ ዕዳዎች ወደ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ የምክርቤት አባላት ሚናቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

በአርብቶ አደሩ አካባቢ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝም አብራርተዋል ።

ክልላዊ የጸጥታ ስራዎች አሁን ላይ የተሻለ ሁኔታ መኖሩን ያብራሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህ የበለጠ ዘላቂ እንዲሆን በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።

በመንገድና ድልድይ ስራዎች ህብረተሰቡን በማስተባበር የመጡ ለውጦችን አጠናክሮ ማስቀጠል ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን የገለጹት ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የክልሉ መንግስት ለመንገድ ጥገና ስራዎች የሚያግዙ 3 ግሬደር ማሽኖችን በመግዛት ለሶስቱ ድስትሪክቶች ማስረከብ መቻሉን አብራርተዋል ።

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በነዚህና በሌሎች ጥያቄዎች ዙሪያ ማብራሪያና ምላሽ የሰጡ ሲሆን የምክርቤት አባላት ሪፖርቱን በሙሉ ድምጽ ጽድቀዋል ።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *