
የሰው ልጅ የሕይወት ጉዞ በዕድልና በትግል የተሞላ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን መርቀዋል፡፡
በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግርም ይህንን አስደማሚ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሌሎች የጥቁር ሕዝቦች ሀገራት ሊሠሩት ቢችሉም÷ የምኒልክ ልጅ፣ የባልቻ ልጅ፣ የገበየሁ ልጅ፣ የአሉላ አባ ነጋ ልጅ መሆን ግን አይችሉም ብለዋል፡፡
ዕድል ከሌለ ትግል ብቻውን ስኬት እንደማያመጣ ጠቁመው÷ኢትዮጵያውያን የታደልነው ድል ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን በሙሉ ዕድለኞች ነን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ዕድለኞች ያደረገን ደግሞ ኢትዮጵያዊ መሆናችን ነው ብለዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡
