



በፌዴራል ስታትስክስ አገልግሎትና በአጋር የልማት ድርጅቶች /UNFPA/ ድጋፍ በክልሉ የመጀመሪያ የሆነው የለማ ክልላዊ ዳታ ቤዝ መሆኑ ተጠቁሟል።
የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሰለሞን አየለ እንደገለፁ የክልሉን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ዲሞግራፊያዊ እንዲሁም የካርታ መረጃዎችን በማዘጋጀት በዳታ-ቤዝ በማደራጀት ለዕቅድ አውጪዎች፣ለውሳኔ ሰጭዎች፣ለፕሮጀክትና ፕሮግራም አዘጋጆች፣ለትምህርትና ምርምር ሥራዎች እንዲሁም ለኢኮኖሚ ዕድገቱ ዕገዛ የሚያደርጉ መረጃዎችን ማቅረብ ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ ዉስጥ ጠንካራ የመረጃ ስርዓት በመዘርጋት አስተማማኝ፣ ትክክለኛና ወጥነት ያለው መረጃ በማመንጭት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎች በሳይንሳዊ መንገድ ታቅደው እንዲፈፀሙ በማድረግ ሰፊ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ህብረተሰቡን ዘላቂና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እርስ በርስ ተመጋግቦ ለማስፈፀም የማክሮ ኢኮኖሚ መረጃዎችን እንዲሰባሰቡ፣ እንዲደራጁ፣ ለተጠቃሚ አመቺ በሆነ ሥርዓት እንዲከማቹ ተገቢውን ሥርዓት መዘርጋትና ተግባራዊነቱን መከታተል አስፈላጊ መሆኑን አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል።
ወቅታዊና ትክክለኛ የስታትስቲክስ መረጃ በማሰባሰብ፣ በመተንተን፣ በማጥራት በዳታ-ቤዝ በማደራጀት የተጠቃሚዎችን እርካታ በማሳደግ መረጃ ፈላጊዎች መረጃው ወዳለበት ቦታ መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት ሆነው መረጃን ተደራሽ ለማድረግ የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ከኢትዮዽያ ስታስትቲክስ አገልግሎት እና ከልማት አጋሮች /UNFPA/ ጋር በመተባበር ክልላዊ ዳታ-ቤዝ /Regional Data Base/ የተቀናጀ አስተዳደር መረጃ ስርዓት /Integrated Management Information System/ማልማት መቻሉን ተናግረዋል።
ዳታ ቤዙን ለማልማት ከክልሉ ቢሮዎች የተወጣጡ ባለሙያዎች በተከታታይ ስልጠና በመስጠት፣ለዳታ-ቤዙ አገልግሎት የሚውል አንድ ሰርቨርና ሁለት ላፕቶፕ ኮሚፕውተር ድጋፍ ድጋፍ በማገኘት የመረጃ ተደራሽነቱን በማስፋት ሲስተሙን በክልል ደረጃ እንዲቀጥል ለማድረግ የክልሉ ዳታ-ቤዝ እንዲዘጋጅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ እነሆ ዛሬ ለማስተዋወቅ በአካል ተገኝተው አስተዋውቀዋል ብለዋል።
በክልሉ ውስጥ ከሚገኙ አስተዳደራዊ መዋቅሮች የሚሰበሰበውን አስተዳደራዊ መረጃዎችን ትክክለኛና ወጥ እንዲሆኑ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት እንዲወስዱ ሲሉ አቶ ሰለሞን አሳስበዋል።
የUNFPA project አስተባባሪ አቶ አለማየሁ ገ/ፃድቅ ስለ የተቀናጀ አስተዳደር መረጃ ስርዓት (Integrated Management Information System) ማብራሪያ ሰጥተዋል።
