የጋንዲዎች ተራራ ላይ ሀይቅ

Spread the love

የጋንዲዎች ተራራ ላይ ሀይቅ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን በአንድራቻ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ከመድናችን አዲስ አበባ 700 ኪ.ሜ ከዞኑ ዋና ከተማ ቴፒ በ35 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡፡

በክልሉ ሸካ ዞን በአንድራቻ ወረዳ በዮክጭጪ ቀበሌ የሚገኝ ነዉ፡፡

ሀይቁ በተራራ ላይ ከመሆኑ በላይ ክብ ቅርጽ ያለዉ መሆኑና ዙሪያዉ ጥቅጥቅ ባለዉ ድንና በቀርከሃ የተከበበ መሆኑን፤ ክረምት ሆነ በበጋ ምንም አይነት የመጠን ልዩነት የማያሳይ መሆኑ ለየት ያደርገዋል፡፡

በተጨማርም የሀይቁ ዙርያ በዩኔስኮ የተመዘገበ ደን ተከቧል፡፡ ጋንዲዎች ሲመጡ ሀይቁን ብቻ ሳይሆን የሸካ ጥብቅ ደንን አብሮ ይጎበኛሉ፡፡

ይህንን ሀይቅ ማልማት የቱሪስት ፍላጎት ለማሟላት ወሳኝ በመሆኑ የዞኑ አስተዳደር ሀይቁ የሚገኝበትን አካባቢ በመሠረተ ልማት ለማስተሳሰር በራሱ በጀት በመመደብ ከዋናዉ መንገድ 3 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ አሰርቷል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *