በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ በመሠረተ-ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ የተመራው የአመራር ቡድን ከዳዉሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጋር የሦስት ወራት ግብ ስምምነት አካሄዱ

Spread the love

ከዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቀጣይ ሥራዎች ዋና ዋና ግቦች ላይ የግብ ስምምነት ተደርጓል።

በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ መሠረተ-ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ እንደገለፁት አመራሩ ከሕዝብና ከመንግሥት የተጣለበትን ኃላፊነት በጊዜ የለኝም መንፈስ በማከናወን የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።

ተግባራትን ቆጥሮ በመሥራት እንዲሁም በመፍጠር፤ በመፍጠን እና በዝላይ ዉጤት ማስመዝገብ መቻል እንደሚገባና ሥልጠናውን ወደ ውጤት መቀየር እንዳለበትም ገልጸዋል።

የትምህርት ለትውልድ ስራዎች በሁሉም ወረዳዎች ሞዴል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ከማስፋፋት አንፃር፣

በቱሪዝም ዘርፉን፣ ሞዴል የሆነ የብልጽግና ህብረትና ቤተሰብ፣ የፓርቲ ህንጻ ግንባታ፤ ከተረጂነት ለመላቀቅ፤ ህገወጥ ኮንትሮባንድስቶች ቁጥጥር ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸው ተብራርቷል።

በዞኑ ያሉት አልሚ ባለሀብቶች በተሠማሩበት በየሥራ ዘርፎቻቸው እንዲያለሙ የድጋፍ እና ክትትል ሥራ በሁሉም አቅም ማጠናከር ይጠበቃልም ብለዋል።

የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው በፈጠራ እና በፍጥነት በዉጤት ሊታጀብ የሚችል የግብ ስምምነት በማካሄድ ሥራ መጀመራቸውን ጠቅሶ የድጋፍ እና ክትትል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪው ከወረዳዎችና ከከተማ አስተዳዳሪዎች ጋር የግብ ስምምነት አካሂደዋል።

የፕሮጀክት እና የፕሮግራም አቅሞችን በአግባቡ በመለየት በማቀናጀት ለዜጎች ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባም አቶ ዳዊት ገልጸዋል።

በስተመጨረሻም የድጋፍ ቡድኑ በዞኑ በተለያዩ መዋቅሮችን ምልከታ ባደረጉት መነሻ አጠቃላይ ለዞኑ አመራር ግብረ መልስ ተሰጥቷል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *