




የክልሉ የአመራር የድጋፍና ክትትል ቡድን በካፋ ዞን በፓርቲና በመንግሥት እየተከናወኑ ያሉት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ድጋፋዊ ክትትልና ምልከታ እያደረገ መሆኑ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት የአመራር ቡድኑ በካፋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በ90 ቀናት በፓርቲና በመንግስት የተቀመጡ ዕቅዶችን ለማሳለጥ እየተደረገ ያለውን የድጋፍ፣ ክትትልና የምልከታ ስራዎችን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገምግመዋል።
በድጋፍና ክትትል ስራዎች በ90 ቀናት በፓርቲና በመንግስት የተቀመጡ ግቦችን ከማሳካት አኳያ የታዩ ጥንካሬዎች፣ ክፍተቶችና ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ግምገማ ተካሂዷል።
በዚሁ ጊዜ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን አመራሩ በክልሉ ያሉትን እምቅ አቅምና ዕድሎች ወደ ሀብትነት ለመቀየር እያረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል ።
አመራሩ የፓርቲ የመንግስት ኢኒሼቲቮችን በግንባር ቀደምትነት በውጤታማነት በመፈጸምና በማስፈጸም ኃላፊነቱን መወጣት በብቃት መወጣት እንደለበት አመላክተዋል።
የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ አሰራሮችን በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
በዚህም ምርታማነትን ለማሻሻል በሚረዱ አሠራሮች ላይ የገለጹት ኩታ ገጠም እርሻ፣የምርጥ ዘርና ማዳበሪያ አጠቃቀም ፣ ሜካናይዜሽን እርሻን በመጠቀም ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የቤተሰብ ብልጽግናን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትጋት ቁርጠኝትን ተግባራት መከወን እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከተግዳሮቶች ለመሻገር በአዲስ የአስተሳሰብ ቅኝትና የአመለካከት እይታ መምራት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ፍቅሬ በየአካባቢው ያሉትን እምቅ አቅሞችና ዕድሎችን ውጤታማ ንቅናቄ በመፍጠር በሁሉም ዘርፍ እመርታ ማስመዝገብ ይጠበቃል ብለዋል።
አደረጃጀቶችን የልማት አቅሞቻችንና መሠረቶች ናቸው ያሉት አቶ ፍቅሬ በዚህም በተግባር ውጤታማ አደረጃጀት እንዲንኖር ማስቻል ይጠበቃል ብለዋል።
የገቢ አሰባሰቡን በተደራጀና ውጤት ተግባራትን በመምራት የህዝቡን የመልማት፣ የማደግና የመበልግ ፍላጎቶች ዕውን ማድረግ ከሁሉም አመራር ይጠበቃል ብለዋል።
የገጠር ሞዴል መንደር፣የገጠር ኮሪደር ፣የትምህርት ለትውልድ ፣የመዘጋጃዊ ቤት አገልግሎት ፣የጤና መድህን ፣ሊለማ የሚችል መሬት ማልማትና የፋይዳ አገልግሎት ሌሎች የተቀመጡ ግቦችን በቅንጂታዊ አንድነት መስራት ይጠበቃል ነው ያሉት።
በተግባር አፈጻጸም ሂደት የታዩ ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማጎልበትና ክፍተቶችን ነቅሶ በመለየት በቀጣይ በሁሉም አካባቢዎች በሁሉም በ90ቀናት የተቀመጡ ዕቅዶችን ለማሳካት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
