በመደመር መንግሥት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ የካፋ ዞን እና የቦንጋ ከተማ እያንሰራራ ነው – ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር)

Spread the love

“የጉባ ብስራቶች፣የመደመር ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የተዘጋጀው የህዝብ ዉይይት መድረክ ተጠናቋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት በኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትርና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፥ በመደመር መንግሥት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሆነ የቦንጋ ከተማ እያንሰራራ ነው ብለዋል።

በህዝቡ የተነሱ የልማት ጥያቄዎች የእቅድ አካል በማድረግ ለመፍታት መንግሥት ቁርጠኛ መኾኑን የገለጹት ዶ/ር ተስፋዬ፥ የተገኙ ለውጦችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በአጽንኦት ተናግረዋል።

በጉባ በክብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተበሰሩ የ30 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ በአንድነትና በኅብረት በመቆም እንዲሁም ሠላማችንን በመጠበቅ የኢትዮጵያ ማንሰራራት እውን ማድረግ ይገባል ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ።

የካፋ ህዝብ፣ የሀገር በቀል የመደመር የዲሞክራሲ ልምምድ የሚያጠናክር የዳበረ ጥንታዊ ስልጣኔ ባህል ባለቤት ነው ያሉት ዶ/ር ተስፋዬ በሁሉም ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ እምርታዊ ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከገባችበት ውስብስብ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቀውስ መታደጉን የገለጹት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል

አቶ ሳዳት ነሻ፥ከዚህ የለውጡ ትሩፋቶች አንዱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መፈጠር መኾኑን ገልጸዋል።

በሀገር ደረጃ መንግሥት ለሠላም ቅድሚያ ሰጥተው እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ ሳዳት፥ ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን የዘመናት ዕዳ እየከፈለ የዜጎችን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማረጋገጥ በትጋት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በመድረኩ የኢትዮጵያን ማንሰራራት በሚያበስሩ እና የጉባ ብስራቶችን ለማሳካት የሚያስችል የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሠላም ተምሳሌት ነው ያሉት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ና የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል አቶ ፍቅሬ አማን፥ ከለውጡ በፊት የፀጥታ ስጋት የነበረባቸው የክልሉ አካባቢዎች አሁን ላይ የልማት ቀጠና ሆነዋል ብለዋል።

የተገኘውን ሠላም በማጽናት በልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ የገለጹት አቶ ፍቅሬ፣ ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ በሁሉም መስኮች ውጤታማ ተግባራት የተከናወኑ ቢሆንም ክልሉ ካለው እምቅ አቅም አኳያ ቀሪ የቤት ሥራዎች እንዳሉት የክልሉ መንግሥት ይገነዘባል ብለዋል።

በክልሉ ቁጠባን መሠረት ያደረገ የሀብት አጠቃቀም በመከተል የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መኾኑን በመጥቀስ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት በማሻሻል፣ ከተሰበሰበው ሀብት ላይ ከፍተኛውን ድርሻ ለልማት መድቦ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በውይይቱ ከኅብረተሰቡ የተነሱ የልማት ጥያቄዎችን በክልሉ አቅም የሚፈቱትን ደረጃ በደረጃ እንዲሁም በፌዴራል መንግሥት በኩል የሚፈቱትን በመለየት እንዲፈታ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *