በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ማኪራ ቡና በቱር ኢትዮጵያ “ላንድ ኦፍ ኦሪጅን” ጎብኝት ተደረገ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡናን ለዓለም ያበረከተች የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ማኪራ ቡናን የቱር ኢትዮጵያ ቡድን ጎብኝቷል።

በኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተመራ ቱር ኢትዮጵያ /Land of Origion/ ቡድን በካፋ ዞን የቡና መገኛ በሆነቹ ዴቻ ወረዳ ማኪራ ጉብኝት አድርጓል ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ከማኪራ ቡኒ መንደር የቡና ምርት በቡና መገኛ እስከ ማኪራ ድረስ በመምጣት የሚገበያዩበት የንግድ አካባቢ ቲፋን መነሻ ያደረገ ጉብኝት ነው የተደረገው።

በመቀጠል በካፋ ዞን ካሉ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ቤተክርስቲያን አንዱ የሆነውን አንድራቻ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ጉብኝት አድርጓል ።

በተመሳሳይ መልኩ የቱር ኢትዮጵያ ቡድን በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የሚገኘውን ጉርጉቶ የተፈጥሮ ድልድይ/የእግዚሄር ድልድይ/ ጎብኝት አድርጓል ።

የቡና ታሪክ ተመራማሪ አቶ ሠለሞን ተክሌ በወቅቱ በሰጡት ማብራሪያ አረቢካ ቡና መገኛ ካፋ ማኪራ ቡኒ እንደሆነች በርካታ የውጭና የሀገር ውስጥ የጥናት ውጤቶች መኖራቸውን አብራርቷል።

በኢትዮጵያ ሀገራችን በደቡብ ምዕራብ ክልል ካፋ የቡና መገኛ መሆኑን በአለም አቀፍ የተሰሩ 22 የሚሆኑ የቡና ጥናቶች እንደሚያረጋግጡም ተናግረዋል ።

በዚህም የቡና መገኛ መሆኑን የማኪራ ቡና DNA ናሙና ተወስዶ መረጋገጡንም ጠቅሰው ከለሎች ዝሪያዎች በተለየ 44 ክሮሞዞም ያላት ብቸኛ ቡና እንደሆነችም ተመራማሪው ሠለሞን ተክሌ ገልጸዋል ።

የካፋ ህዝብ ተፈጥሮን ጠብቆና ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ የሚኖር በመሆኑ ጥቅጥቅ የጫካ ቡናን ከደኑ ጋር ጠብቆ ማቆየታቸውንም ጠቅሰዋል ።

ከጎብኚዎች መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት በአጠቃላይ ባዩት የቡና ታሪክ እና በተፈጥሮ ሀብት መደነቃቸውን ገልፀው የተመለከቱትን ገጽታ ለዓለም የሚያስተዋውቁ መሆኑን ማረጋገጣቸዉን የካፋ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *