

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የ1 ነጥብ 466 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ልማት ትብብር የሚውል የ1 ነጥብ 466 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጓል።
ድጋፉ ለአምስት ዓመት ለጤና ዘርፍ ዘላቂ ልማት እና የጋራ ኢንቨስትመንት ማጠናከሪያ ትብብር የሚውል ነው።
የመግባቢያ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ፈርመዋል።
ድጋፉ በኢትዮጵያና አሜሪካ ትብብር ታሪካዊ የተባለለት ሲሆን የአዲሱ የትብብር ምዕራፍ የጠበቀ ግንኙነት ማሳያ እንደሆነም ተነስቷል።
120 ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አሜሪካ ወዳጅነት በተለያዩ የትብብር መስኮች ሲገለጥ መቆየቱ ይታወሳል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
