




ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዳግማዊ ዓድዋ በመሆኑ መላው አፍሪካዊያን ሊያዩት የሚጓጉለት ትልቅ የቱሪዝም መስህብ ነው ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታው ስለሺ ግርማ ተናገሩ።
ሚኒስትር ዴኤታው ይህን ያሉት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዘጋጅነት በጉባ እየተካሄደ በሚገኘው ስለ ኢትዮጵያ የውይይት መድረክ ላይ ነው።
መንግሥት የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ በሰጠው የፖሊሲ ትኩረት እና የፖለቲካ ቁርጠኝነት ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦው በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን አቶ ስለሺ ተናግረዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚገኝበት የጉባ አካባቢ ደግሞ ድንቅ የተፈጥሮ ሀብት ያለበት በመሆኑ ዘርፉን ለማሳደግ ሚናው የላቀ ስለመሆኑ አንስተዋል።
ግድቡ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ሊጎበኘው የሚመኘው፣ የራሱ ታሪክ ያለው ቅርስ፣ ድንቅ የግንባታ ጥበብ የታየበት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ሲሉ ገልጸውታል።
ከ70 በላይ ደሴቶች እና ከፍተኛ የሆነ የዓሣ ሀብት ያለው በመሆኑም ከፍተኛ ገቢ ማስገኘት የሚችል ስለመሆኑም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
