




በሲዝ ከተማ አስተዳደር”የጉባ ብስራቶች የመደመር ትሩፋቶች”በሚል ህዝባዊ ውይይት አየተካሄደ ይገኛል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ እንደገለፁት በብልፅግና በፓርቲያችን መሪነት በሀገራችን በርካታ ስራዎች የተሰሩበት፣በቀጠናው ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን ያስቻለ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻልና ከድህነት የማላቀቅ ስራ በስፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግስት በሁሉም ደረጃ የሀገራችንን መልካም ገፅታ ሊያሳዩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ፣የመጀመር ፣ የተረጋጋ ሀገረ መንግስትና ለሁሉም የተመቸ የፖለቲካ አስተዳደር እንዲሰፍን የሚያስችሉ ስራዎችን በመስራት ትልቅ እምርታ እየታየ መሆኑን ወ/ሮ ህይወት ጠቁመዋል።
የህዳሴ ግድብን በልጆቿ እልህ አስጨራጭ ጥረት በማጠናቀቅ ለሌሎች ሀገራትም ኢትዮጵያ ተምሳሌት መሆን መቻሏን ጠቁመዋል።
የራስን ችግር በራስ መፍታት የሚያስችልም በርካታ ተግባራት እያከናወነ ያለ መንግስት ነው ሲሉም ወ/ሮ ህይወት ተናግረዋል።
ከህዝብ ጋር በመወያየት ድሎችን ማጠናከር ለክፍተቶች በጋራ መስራትን አጠናክሮ እየሄደ መሆኑን ህዝባዊ ውይይቶች አመላካች ናቸው ብለዋል።
የሲዝ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታሪኩ ደሳለኝ እንደገለፁት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ህብረተሰቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ህዝባዊ የውይይት መድረኮች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ።
የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ በርካታ ውጤታማ ሥራዎች በመሠራት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በውይይት መድረኩ የሲዝ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታሪኩ ደሳለኝ የመነሻ ሰነድ እያቀረቡ እንደሚገኙ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
