የቀደምት ዳውሮዎች ችሎት አዳራሽ የነበረው “ካቲ ሁሉቆ” ዋሻ

Spread the love

ካቲ ሁሉቆ ዋሻ በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሣ ወረዳ ሎማ ሻምቢ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከወረዳው ዋና ከተማ በስተ ደቡብ ምዕራብ በ 25 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

ከ 18ኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነገስታት ማህበራዊ፣ አስተዳደራዊ እና ሌሎች የእምነት ጉድለት የፈፀሙ ግለሰቦችን ምህረት የሚሰጡበት ስፍራ እንደሆነ የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ።

አጥፊዎች ምህረት ለመቀበል ሲመጡ በመግቢያው በር በኩል መጥተው ከንጉሱ ይቅርታና ዳኝነት ከተቀበሉ በኃላ በመውጫው በኩል ይወጡና ቤተሰቦቻቸው ይቀበሉዋቸውና ወደ ወንዝ ወርደው ታጥበው ይመለሳሉ።

ዋሻው ከታችኛው ስፍራ 150 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን 1ሺህ 500 ካሬሜትር ስፋትም አለው።

ይህ ስፍራ ከዋነኛው አገልግሎቱ በተጨማሪ በጦርነት ወቅት ለመከላከያነትም እንዳገለገለ የታሪክ አዋቂው መ/ር ተስፋዬ ሽበሺ ያስታውሳሉ።

ዋሻውና በዙሪያው ያለው 3 ሄክታር መሬት ወሰን ተክብረውለት አስፈላጊ ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን የሎማ ቦሳ ወረዳ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሀብታሙ ክፍለ ተናግረዋል።

ይህ ስፍራ እንደ ሌሎቹ የሀገራችን መስሂቦች ለምተው ለጉብኝት ክፍት እንዲሆን ህብረተሰቡን በማሳተፍ የመንገድ ስራ እየተፋጠነ መሆኑን ዋና ተጠሪው አክለው ገልጸዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎችም ተቀናጅተው ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ እያደረጉ እንደሆነ መመልከት ተችሏል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *