




የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው የአሜሪካውን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳውን ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ የሐሳብ ልውውጥ አድርገዋል።
ኢትዮጵያና አሜሪካ ለ120 ዓመታት የዘለቀ ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ የዛሬው ውይይትም ይህንን ስትራቴጂካዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ነው ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
