





ዩኒቨርሲቲው ከምርምርና ትምህርት ስራ ጎን ለጎን በተለያዩ ማሕበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች በማከናወን ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑም ተጠቁሟል።
በተለይም ጧሪ ደጋፊ የሌላቸውን አረጋውያን ለመደገፍ የአረጋውያን መንደርን በማመቻቸት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡
የትናንት ባለታሪክ እና የሀገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያንን ከወደቁበት በማንሳት ዩኒቨርሲቲው ባስገነባው መንደር እየተንከባከበ መሆኑን ገልጸዋል።
ተቋሙ በተለያዩ የማሕበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች ላይ እየተሳተፈ አካባቢያዊ ሀብቶችን በማልማት ለሀገር ብልፅግና ሚናውን እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡
በዋናነት በግብርናው ዘርፍ የምርምር ተግባራትን እያከናወነ ውጤት እንዲመዘገብ ምቹ መደላድልን መፍጠሩን አንስተው÷ በመሰል ተግባራት ላይ የሚከውነውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጧል ሲል ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።
