የካፋ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀምሯል::

Spread the love

ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባኤው ያለፈውን 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት 25ኛውን ጉባኤ ቃለጉባኤ መርምሮ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ነው የጀመረው::

በመቀጠል ምክር ቤቱ የዞኑን ዋና አፈ ጉባኤ ሹመት ያፀደቀ ሲሆን በዚህም ክብርት ወ/ሮ አሚናት ሀሰን የካፋ ዞን ዋና አፈጉባኤ እንዲሆኑ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የቀረበውን የሹመት ፕሮፖዛል ተቀብሎ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ጉባኤ ተጀምሯል::

የዞኑ ምክር ቤት ጉባኤ በሚኖረው ቆይታ የዞኑን አስፈፃሚ ተቋማት የ2018 ዓ/ም የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና የከፍተኛ ፍ/ቤት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ በመወያየት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል::

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ የ2018 ዓ/ም የመጀመሪያ 6 ወራት የአስፈፃሚዎችን ሪፖርት እያቀረቡ ናቸው::

ምክር ቤቱ በነዚህና በሌሎች ተጨማሪ አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይቶ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን እንደምያስተላልፍም ተመላክቷል ::

በጉባኤው የምክር ቤቱ አባላት የተቋማት ማናጅመንት አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲል የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *