የቀጣይ ድጋፍ አቅጣጫን ለመለየት ትኩረት ያደረገ የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች ጉብኝት

Spread the love

የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) መሪነት፣ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO)፣ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO)፣ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO)፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ (OCHA) እና የሕፃናትን መብት፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ንጹህ ውሃ እና መከላከያ ለማሻሻል በዓለም አቀፍ የሚሰራው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UNICEF) የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ በካፋ ዞን እየተተገበሩ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጉብኝት አድርገዋል።

የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የሚገኘው የአባይነሽ ፋርም የእንስሳት እርባታ እንዲሁም በዞኑ ዴቻ ወረዳ በሃ ላንድ የቡና እርሻ ልማት የሥራ እንቅስቃሴን ተመልክቷል።

እንዲሁም በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ የተቋቋመው የዲንቻ የመንግስት ሻይ ችግኝ ብዜት ጣቢያ ሌላኛዉ የጉብኝቱ አካል ነው።

የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች የልማት ሥራዎች ጉብኝቱ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን በተግባር በመመልከት የቀጣይ ድጋፍ አቅጣጫን ለመለየት ዓላማ ያደረገ ነዉ።

በነገው ዕለትም የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች ከክልሉ መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ የቀጣይ ድጋፍ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *