ሉዓላዊነት እና ድምፅዎ፤ የማይነጣጠሉ የሀገር ምሰሶዎች

Spread the love

ሀገር በዜጎቿ ድምፅና እውቅና የምትጸና ናት። ድምፅ መስጠት “የዚች ውብ ምድር ባለቤት እኔ ነኝ” ብሎ በኩራት የመመስከር ያህል ነው።

ሉዓላዊነት በወረቀት ላይ የሚሰፍር ቃል ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎች ተሳትፎ የሚረጋገጥ የባለቤትነት ዋስትና ነው።

ምርጫ በመራጭና በተመራጭ መካከል የሚደረግ የቃል ኪዳን ትስስር ነው። “እኔ መርጬሃለሁና ልትሰማኝ ይገባል” የሚል የሞራል ልዕልናን በመፍጠር፣ መሪዎች ለሕዝብ ፍላጎት ተገዥ እንዲሆኑ ያስገድዳል።

ዛሬ የምንሰጠው ድምፅ ለልጆቻችን የምናወርሰው የታሪክ አቅጣጫ ነው። ለትውልድ የሚሆን የሰላምና የልማት ጎዳና በራሳችን እጅ የምንቀርጽበት ትልቅ ዕድል ነው።

በምርጫ መሳተፍ መብት ብቻ ሳይሆን የዜግነታዊ ግዴታም ነው። ዳር ቆመን ሳንወሰን ድምፃችንን ከፍ አድርገን የተሳትፎ ሚዛኑን ልናስተካክል ይገባል።

የሀገር ህልውና የሚጸናው በብዙኃኑ ንቁ ተሳትፎ እንጂ በጥቂቶች ጩኸት አይደለም። የእርስዎ ድምፅ የነገዋ ኢትዮጵያ የቅኝት መጀመሪያ ነው። ኑ! በምርጫው በመሳተፍ የበኩላችንን እናበርክት!ኢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *