




በከተማዋ እየተተገበረ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ የከተማዋን ገፅታ በእጅጉ የቀየረ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ነዋሪዎቹ ከተማ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪ የሆኑት ኮማንደር ታረቀኝ ታፈሰ ከዚህ ቀደም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለረዥም ጊዜ በከተማዋ መኖራቸውን ጠቁመው አሁን እየተሰራ ያለ ኮሪደር ልማት ለመኖሪያ ምቹ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይ ዋናው መንገድ ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ ዜጎች ሲቸገሩ መቆየታቸውን የገለጹት ኮማንደር ታረቀኝ አሁን ላይ ተማሪዎች በነፃነት ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ፤ ነዋሪዎች በምቹ ከተማ እንዲንቀሳቀሱ አስችሏል ብለዋል።
በተከናወነ የኮሪደር ልማት ስራ ህዝብ ተደስቷል ያሉት ኮማንደር ታረቀኝ ልማቱ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዜጎች ከመንግስት ጎን በመሆን የልማት ተሳትፏቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ሌላው የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መለሰ ናስር ኮሪደር ልማት ስራው በከተማዋ ሁሉን ያማከለ የወሰን ማስከበር እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታን አስፋፍቷል ብለዋል።
በሚዛን አማን ከተማ እየተከናወነ ያለ ይህ የኮሪደር ልማት ኢንሼቲቭ ከተማዋን ምቹ የስራ እና የመኖሪያ ማዕከል እያደረጋት በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የኮሪደር ልማት ስራው የከተማ ዕድገት ከማነቃቃት ባለፈ በከተማዋ እያታየ ላለው ሁሉአቀፍ ለውጥ የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን የገለጹት ሌላው የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ተፈሪ ናቸው ሲል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።
