የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

Spread the love

በመድረኩ ላይ የዞኑን ወቅታዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በመፈተሽ፣ የአመራሩን ቁመና የማጥራት ስራ ትኩረት እንደሚሰጠው ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ዋና አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ወንድሙ ኩርታ ዞኑ በክልል ደረጃ የተሻለ አፈፃፀም እያስመዘገበ ያለ ዞን መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይሁን እንጂ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ህዝባዊ አገልጋይነትን ለማረጋገጥ አመራሩን በሦስት ዋና ዋና ነጥቦች መፈተሽ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የፓርቲ ኢኒሼቲቭ ስራዎች ላይ የሚታየውን ወጣ ገባ የአፈፃፀም ክፍተት በማረም አመራሩ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የሚጠበቅበትን ቁመና እንዲላበስ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ በበኩላቸው ባለፉት ጊዜያት የተከናወኑ የሪፎርም (የለውጥ) ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህንኑ ውጤት ይበልጥ ለማሳደግ የአመራር የማጥራት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለግልጽነትና ለተጠያቂነት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ይህ የግምገማ መድረክ አመራሩ ባለፉት ስድስት ወራት የነበሩ ጥንካሬዎችን እንዲያስቀጥልና በድክመት የታዩትን ደግሞ በዝርዝር በመለየት በቀጣይ ግማሽ ዓመት ለላቀ ውጤት እንዲዘጋጅ የሚያስችል ነው ተብለዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *