




መድረኩ ከፓርቲው እሳቤና መርሆዎች ተነስቶ ተቋማት የተጣለባቸውን የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በአመራር መሪነት የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር የሚገመግም መሆኑ ተገልጿል።
የግምገማ መድረኩን እየመሩ የሚገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ እንደገለጹት የመድረኩ ዋና ዓላማ የፓርቲውን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል እና የታዩ ክፍተቶችን በግልጽ በመወያየት የአመራሩን የመፈጸም አቅም ማሳደግ መሆኑን ገልጸዋል።
የአመራር ምዘናው ጠንካራ ተቋም በመገንባት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚረዳ ሲሆን አመራሩ የፓርቲውን ተልዕኮዎች በብቃት በመፈጸም ለህዝቡ ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንዳለበትም ጠቁመዋል።
ምዘናው ጠንካራ የአመራር አሀድ በመፍጠር የመንግሥትና የፓርቲ ኢንሼቲቮችን እንዲሁም መደበኛ ተግባራትን በተሻለ መልኩ በመፈጸም ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ የመልካም አስተዳደርና የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች በዝርዝር እንደሚገመገሙ ገልጸዋል።
እንዲሁም ምዘናው የአመራር አፈጻጸምን በግልጽ፣ ወጥና ፍትሃዊ መንገድ በመፈጸም የፓርቲውን የአመራር ጥራትና ውጤታማነት ለማሳደግ እና ለቀጣይ ተልዕኮ እንዲዘጋጅ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።
በሂደቱም በዝግጅትና በተግባር ምዕራፎች የታዩ ጥንካሬዎችና ውስንነቶችን በመለየት ለቀጣይ ሥራዎች መሻሻል መሠረት እንደሚሆን ተገልጿል።
ግምገዉ ለሁለት ቀናት የሚቆይና እስከታችኛዉ መዋቅር የሚቀጥል ይሆናል።
ዛሬ በተጀመረዉ መድረክ የሸካ ዞን አጠቃላይ አመራር፣ የወረዳ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የግምገማና ምዘና መድረኩን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጫናቸው ወንድሙ በጋራ እየመሩ ይገኛሉ ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
