አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ::

Spread the love

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላርስ ራስሙሰን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሮቹ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በአህጉራዊና ቀጣናዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት በሚያስችላቸው ሁኔታዎች ላይም ውይይት አድርገዋል።

ኢትዮጵያና ዴንማርክ በልማት ትብብር፣ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል፣ በሰብአዊ እርዳታና በሌሎች መስኮችም በጋራ እየሰሩ መሆኑ ይታወቃል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *