





ሀገራዊ ለውጡ የተበሰረበትና 8ኛ ዓመት፤ የለውጡ ፍሬዎችን የሚያንፀባረቁ፤ የሚዘክርና የአገራዊ አንድነትን ጥንካሬ የሚያሳይ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብዝሀ ከተሞች አንዱ በሆነው በቦንጋ በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች ተካሂዷል።
ያነጋገርናቸው የድጋፍ ሰልፉ ታዳሚ አመራሮች መጋቢት 24 ባመጣቸውና በለውጡ መንግስት በተመዘገቡ ድሎች ዙሪያ አስተያየታቸውን ስጥተዋል ።
የክልሉ የመንግስት ረዳት ተጠሪ የሆኑት አቶ በላይ ተሰማ መጋቢት 24 በሀገራችን ታርክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ከመደረጉም በላይ ክልሉ አንዱ የለውጡ ፍሬ ማሳያ ነው ብለዋል።
አክለውም መጋቢት 24 በሀገራችን የነበሩ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ስብራቶች የመጠገንና አስተሳሳሪ ገዥ ትርክት በመገንባት ብዙሃነትን በአግባቡ ለማስተናገድና አካታችነትን በማረጋገጥና የፖለቲካ ስነ ምህዳሩን ለማስፋት በለውጡ የተደረገው ጥረት አመርቂ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን አንስተዋል።
በመሆኑም አመራና አባሉ ብሎም አጠቃላይ የክልሉ ህዝብ የተጀመረውን የለውጥ ጮራ ከግብ ለማድረስ እና ብልጽግና ፓርቲ በዲፕሎማሲው መስክ የጀመረውን የባህር በርን የማስመለስ ጥረቶችን እንዲደግፍ አሳስበዋል።
የክልሉ የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አንድነት አሸናፊ ዕለቱ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት አካታች የፖለቲካ ስርዓት ይፋ የተደረገበት ቀን መሆኑን ገልጸዋል።
በፊት የነበሩ የፖለቲካ ስብራቶች በአካታችና መደመር ፖለቲካ ዕሳቤ ተቃኝቶ ምህዳሩ የሰፋበት መሆኑን አንስተው፤ ዴሞክራሲን ለማስፋትና የህግ በላይነትን ለማረጋገጥ የፍትህና ፀጥታ ተቋማት ሪፎርም መደረጉን፤ አንዳንድ ህጎችም ጭምር መሻሻላቸውን አብራርተዋል።
ሌላው አስተያየት ሰጪው የክልሉ የዴሞክራሲ ስርዓት ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፍ አቶ ግርማ ባሻ የነበረውን አፍርሶ ከዜሮ የመጀመር የፖለቲካ ባህልን በመሻገር መልካም ወረቶችን በማስቀጠል የተለያዩ ስብራቶችን በመጠገን ለውጡን የጀመረበት ቀን መሆኑን አንስተዋል።
የመጣው ለውጥ በኃይል ሳይሆን በህዝቡ ፍላጎት፣ በዴሞክራሲያዊ ሂደትና በህገ መንግስቱ መሠረት ሽግግር መደረጉን በማስታወስ፤ ከአገላይነት አካታች ወደ ሆነ ስርዓት በመሸጋገር በህዝቦች ዘንድ የሀገር ባለቤትነት ስሜት እንዲፈጠር ማድረጉን ገልጸዋል።
ሰልፉ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዘርፌ ብዙ ትሩፋቶችን ከመዘከርም ባሻገር ክልላዊ አንድነትን ለማጠናከር ሚናው የጎላ መሆኑን ያነሱት አስተያየት ሰጪዋ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሪት ለምለም አምሳሉ ናቸው።
አክለውም የተጀመረውን የለውጥ ጉዞን ለማስቀጠል ህብረተሰቡ ባለበት ሁሉ ለሠላም ዘብ መቆምና በተሰማራበት ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባ በማሳሰብ በቀጣይ በሚደረገው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ካርድን በጊዜ በመውሰድ ድምፅ ለመስጠት እንዲዘጋጁ ጠይቀዋል።
የካፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ኃይሌ የውጡ መንግስት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና ያለበት የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተጠናቀቀበትና ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶች ተጀምሮ በፍጥነትና በጥራት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ መስራቱን ገልጸዋል።
በመሆኑም የመጡ ውጤቶችን ለማስቀጠል ቀጣይ ጠቅላላ ምርጫው ሠላማዊ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊነት ያለው፤ የብልጽግና ፓርቲ መንግስትን መመሥረት የሚያስችል ድምፅ እንዲያገኝ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የቦንጋ ከተማ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍረው አበበ ህዝብ ዘንድ ለሚነሱ በክልል የመደራጀት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠ መሆኑን አንስተዋል።
ከተሞችን አረንጓደ፣ ውብ ፣ፅዱና ለዜጎች በኮርደር ልማት አማካኝነት ምቹ ከማድረግም ባሻገር የከተሞችን የፕላን ጥሰት ችግሮች ለመፍታ ውጤታማ ስራ የተሰራበት መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም አስተያየት ሰጪዎቹ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልላችን ያሉ የቱሪዝም ጸጋዎች ወደ ተጨባጭ ለውጥ ለመቀየር የሚያስችሉ ሥራዎች መሰራቱን በማስታወስ፤ በክል የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ለማስቀጠል በአንድነት መነሳት አለበት ብለዋል።
በጌታሁን ግርማ
