





የከተማ ወጣቶች የተራዘመውን የመራጮች ምዝገባ ጊዜ በመጠቀም ካርድ ከመውሰድ በተጨማሪ የምርጫ ሂደቱ ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸዉን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
ያነጋገርናቸው ወጣቶቹ የምርጫ ካርድ መዉሰድ አንድ ለመምረጥ በህገ መንግስቱ መሰረት የተሰጠውን የዜጎች መብትና በሀገር ዕጣ ፈንታ ከመወሰን ባለፈ የሀገር ፍቅር መገለጫ መሆኑንም ተናግረዋል።
በከተማ አስተዳደር ጌና በር ምርጫ ጣቢያ የተመዘገቡ ወጣቶች በምርጫው ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት ዝግጁ መሆናቸውንም አብራርተዋል።
ወጣቶቹ የተራዘመውን የመራጮች ምዝገባ ጊዜውን በመጠቀም የምርጫ ካርዳቸውን መዉሰዳቸውን እንዲሁም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሰጠው 14 ተጨማሪ ቀናት በተለያዩ ምክንያት ካርድ ላልወሰዱ ሰዎች ተጨማሪ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።
የወጣቶች ተሳትፎ ለዲሞክራሲ ስርዓቱ መጠናከር ትልቅ አቅም እንደሆነና የሀገር ፍቅር መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ወጣቶች እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል የታርጫ ከተማ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
