ለ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ምቹነትን ለመፍጠር መጠነ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ነው ፦አቶ ነጋ አበራ

Spread the love

የክልሉ የምርጫ አብይ ኮሚቴ የኢንስፔክሽን ቡድን የሱፐርቪዥን አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው።

በአፈጻጸም ግምገማ ላይ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንቢታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንዳሉት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ነፃ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መጠነ ሰፊ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ምቹነትን ለመፍጠር በክልሉ የምርጫ ኮሚቴ የኢንስፔክሽን ቡድን ተቋቁሞ ወደዞኖች ወርዶ ባደረጉት ክትትል የእስካሀኑ ቅድመ ምርጫ ተግባራት አበረታች እንደሆነ አንስተዋል።

የኢንስፔክሽን ስራዎች እየተከናወኑ ያሉት ስራዎች ከስኬቶች ለመማር፣ ክፍተቶችን ለማረምና ተሞክሮዎችን ለመቀመር ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር በመሆኑ እንደ ክልል በ7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በጠንካራ አደረጃጀቶችን የመራጮች ምዝገባን በክልሉ የታቀደውን እቅድ ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት የምርጫ ህጉን በተከተለ መልኩ በትጋትና ቁርጠኝነት መስራት ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *