ምርጫ የህዝብ ፍላጎት የሚገለጽበት ከፍተኛ ሀገራዊ ሂደት በመሆኑ ሁሉም አካላት በህግ መሠረት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን አስታወቀ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስነ-ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን በምርጫ ስነምግባር እና በሀብት ምዝገባ ዙሪያ ለስር መዋቅሮች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ እንደገለጹት፤ የስልጠናው ዋና ዓላማ የምርጫ ሥነ_ምግባር መመሪያን በጥልቀት በመረዳት ለመተግበር የሚያስችል አቅም ለመገንባት ያለመ ነው።

7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በክልላችንና በፌዴራል ደረጃ የሚካሄድ ትልቅ ሀገራዊ ሂዳት ነው ያሉት ኮሚሽነር ሙሉሰው ይህም ሂደት በቅዶመ ምርጫ፣ በዕለተ ምርጫ እና በድህረ ምርጫ ወቅት የሚካሄዱ ወሳኝ ደረጃዎችን ያካትታል ብለዋል።

ለዚህም በእያንዳንዱ ደረጃ የሥነምግባር መመሪያዎችን በጥብቅ መከተል፣ የፀረሙስና መርሆዎችን ማስፈፀም እና ሂደቱ ነፃ፣ ኢፍትሃዊ እና ግልጽ እንዲሆን መስራት የሁሉም ኃላፊነት ሊመሆን እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በቅድመ ምርጫ ዝግጅትን በጥንቃቄ ማካሄድ፣ በዕለተ ምርጫ ሂደቱን በፍትሃዊነት መቆጣጠር፣ የድህረ ምርጫ ውጤቶችን በግልጽነት በማረጋገጥ የምርጫ ስኬት መሠረት ነው ያሉት ኮሚሽነር ሙሉሰው ።

በምርጫ ሂደት ውስጥ ሥነምግባርና ፀረሙስና መርሆዎችን ማክበር የዴሞክራሲ መሠረት እና የህዝብ እምነት መገንቢያ መሆኑንና የህዝብ ፍላጎት የሚገለጽበት ከፍተኛ ሀገራዊ ሂደት ስለሆነ ሁሉም አካላት በህግ መሠረት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ገልጸዋል።

ማንኛውም የግል ወይም የፖለቲካ ጥቅም ከህጋዊ ሂደት እንዳይወጣ መከላከልን ይጠይቃል ያሉት ኮሚሽነር ሙሉሰው ከሥልጣና በኋላ የተገኘውን እውቀት ወደ ታችኛው መዋቅር በተዋቀረ መልኩ ማስተላለፍ፣ የሥነምግባር መመሪያዎችን በጥብቅ ማስፈፀም እና ማንኛውም ጥሰት በፍጥነት መከላከል እንደሚጠበቅ አንስተዋል።

በስልጠና መድረኩ በአሁኑ ሰዓት በምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ሰነድ በኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር በሆኑት በአቶ ታደሰ አይበራ እየቀረበ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑን ከወጣው መርሐ ግብር ማወቅ ተችሏል።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *