በክልሉ የሕዝቡን ችግር በማድመጥ ምላሽ የመስጠቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሰ በብልፅግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤት የቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ጋር በቀጣይ ተልዕኮዎች ዙሪያ በቦንጋ ከተማ የተካሄደው የምክክር መድረክ ተጠናቋል።

በምክክር መድረኩ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም በመገምገምና በቀጣዩ ጊዜያት መፈጸም በሚገባቸው ተልዕኮዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

የምክክሩ ተሳታፊ የሁለቱ ክልል ምክር ቤት የሕዝብ ተወካዮች ፤ የክልሉ ሕዝብ የዘመናት በክልል የመደራጀት ጥያቄ መመለስ የተቻለው በብልጽግና ፓርቲ ዘመን ነው ያሉት።

ይህም እንደክልል የመደመጥ ዕድል የተረጋገጠበት ነው ያሉት ተወካዮቹ፤ በዚህም ፓርቲው የሕዝብን ችግር ወርደው በማዳመጥ የልማት ተደራሽነት በማረጋገጥ ሕዝብን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም አስረድተዋል።

የተመዘገቡ ውጤቶች እንዲቀጥሉና ቀሪ የሕዝብ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ከሕዝቡ ጋር ወርደው በመነጋገር ምላሽ እንዲሰጥ በትኩረት እንደሚሰሩ የሁለቱ ምክር ቤት ተወካዮች አንስተዋል።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር),ባለፉት ጥቂት ዓመታት የክልሉ አቅም በፈቀደው ልክ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለህዝብ አገልግሎት ማብቃት መቻሉን ተናግረዋል።

በዚህም አመራሩ በቀጥታ እስከ ቀበሌ ድረስ በመውረድ የህዝቡን ጥያቄዎች እንዲያዳምጥና ተጨባጭ ምላሽ እንዲሰጥ ተደርጓል ነው ያሉት።

ቀጣይ ከሕዝቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የአመራሩን የመፈጸምና የማስፈጸም የበለጠ በመገንባትና የታችኛውን መዋቅሮችን ማጠናከር ለነገ የማይባል ተግባር ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

በክልሉ የሕዝቡን ችግር በማድመጥ ምላሽ የመስጠቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የተናገሩት ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዚህም የሁለቱ ምክር ቤት ተወካዮች ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን፤ በክልሉ ባለፉት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች በመደመር እሳቤ ውጤታማ ስራዎች የተከናወኑበት በብልጽግና ፓርቲ ዘመን ነው ብለዋል።

​ክልሉ ካለው ሰፊ አቅም አንጻር ገና ብዙ መስራትና መልፋት እንደሚጠይቅም ያነሱት አቶ ፍቅሬ አማን፤ በሚቀጥሉት 5ዓመታት ክልሉ አሁን ካለበት የዕድገት ደረጃ እጥፍ እንዲያድግ በትኩረት መሥራት ይገባል ብለዋል።

በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በተቀናጀና በተደራጃ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አንስተዋል አቶ ፍቅሬ አማን።

ከሁለቱ ምክር ቤት ተወካዮች ጋር የተደረገወሰ የምክክር መድረኩ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን በግልጽ ለይቶ ለማስቀመጥ፣ የህዝብ ጥያቄዎችን ለይቶ ለመረዳትና ዕጩዎች በተቀናጀ መንገድ እንዲሰሩ የጋራ መግባባት መፍጠር የተቻለበት ነዉ።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *