በኢፌዲሪ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ የተመራው የሱፐርቪዥን ልኡካን ቡድን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል።

Spread the love

ሱፐርቪዥን ቡድኑ በተመረጡ 17 የትኩረት መስኮች በተለይም ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ነው በዞኑ ድጋፍና ክትትል ያደረገው።

በዚሁ መሠረት የተግባራት አፈፃፀም ያሉበትን ደረጃ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ወርዶ ምልከታ አድርጓል።

ልዑኩ በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ አሩሲ አንገላ ቀበሌ በ195 ሄክታር በዘመናዊ መስኖ የለማ የበጋ ስንዴ እንዲሁም በወረዳው የአሩሲ ባላ ቀበሌ በኩታ ገጠም ዜዴ በ72 አርሶ አደሮች እየተሰራ ያለውን የእንስሳት እርባታ ሥራዎችንና የወተት መንደር ተብሎ የሚጠራውን ተግባር ተመልክቶታል።

በዞኑ ታርጫ ከተማ አስተዳደር በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰራ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታም ምልከታ አድርጓል።

በዚሁ ወቅት በኢፌዲሪ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ እንዳሉት የብልጽግና ፓርቲ ሰውተኮር መሆኑን በተጨባጭ የሚያረጋግጡ እውነታዎች እየተከናወኑ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በዞኑ ያሉ እምቅ የመልማት አቅሞች ለህብረተሰቡ ዘላቂ ተጠቃሚነት እንዲውሉ ለማስቻል ህብረተሰቡን ያሳተፈ ሥራ ይበልጥ እንደሚሰራም አብራርተዋል ።

በሪፖርቱ የታዩ ጠንካራ እና ደካማ አፈፃፀም በመገምገም ጠንካራ አፈፃፀሙ ተጠናክረው እንዲህ ቀጥሉ እንዲሁም በጉድለት የተገመገሙ ነጥቦችን ተለይቶ በቀጣይ መስተካከል እንዳለበትም በውይይቱ ተጠቁሟል።

በሚኒስትሯ የተመራው የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በክልሉ ከዳውሮ ዞን እና ኮንታ ዞን አመራሮች ጋር የጋራ ውይይት ያደረገ ሲሆን በጥንካሬ የተለዩ ተግባራት ይበልጥ እንዲጎለብቱ እንዲሁም ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮች በቀጣይ ታቅዶ እንዲሰራ ተገልጿል።

በውይይቱ ወቅት በዞኑ ከዋካ ኢሠራ የሚገነባው የአስፖልት መንገድ በአፋጣኝ እንዲጀመር፣ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የዳውሮ ታርጫ ካምፖስ ወደ ዩኒቨርስቲ ደረጃ እንዲያድግ፣ የመብራት፣ የባንክ እና የቴሌ ተደራሽነት ላይ መንግስት ትኩረት እንዲያደርግ ጥያቄ ቀርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *