የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ያልመለሱ 565 ግለሰቦች የስም ዝርዝር ይፋ አደረገ::

Spread the love

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በሂሳብችሁ ከተቀመጠ ገንዘብ ውጭ በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዳችሁ ግለሰቦች በፈቃደኝነት ሂሳባችሁ በሚገኝበት ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ወይም ዲጂታል የክፍያ ዘዴን በመጠቀም ገንዘቡን እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመላሽ እንዲያደርጉ መጠየቁ ይታወሳል።

በዚህ መሰረት 14441 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ተጠቅመው የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መመለሳቸውን ባንኩ አስታውቋል።

ሆኖም ከዚህ በታች ስማቸው፣ የሂሳብ ቁጥራቸው እና ሂሳባቸው የሚገኝበት ቅርንጫፍ የተዘረዘረው 565 ግለሰቦች ባንኩ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ አለመመለሳቸውን ባንኩ አስታውቋል።

ባንኩ ቀደም ሲል ባስጠነቀቀው መሠረት ወደ ቀጣዩ ሕጋዊ እርምጃ ከማለፉ በፊት ገንዘቡን በአፋጣኝ እንዲመልሱ አንድ ተጨማሪ ዕድል በመስጠት እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ገንዘቡን በሚመልሱት ላይ በባንኩ በኩል ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃ እንደማይኖር አረጋግጧል።

ነገር ግን እስከተጠቀሰው ቀን ገንዘቡን ያልመለሱ ካሉ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ሙሉ ስማቸውን፣ ፎቶዋቸውን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን በመጥቀስ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት በማሳወቅ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በተጨማሪም ከሕግ አካላትና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ቀጣይ የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔርና የአስተዳደር ሕጋዊ እርምጃዎች እንደሚወሰድ ለመጨረሻ ጊዜ አሳስቧል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *