የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በቦንጋ ከተማ ስልጠና መስጠት ጀመረ::

Spread the love

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በልዩ ሁኔታ ለተመረጡ ኢንተርፕራይዞችና ባለሀብቶች ለ 5 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና በቦንጋ ከተማ መስጠት ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው አበራ በዙም ባስተላለፉት መልዕክት የአሁኑ ስልጠና ከዚህ ቀደም ከነበረው የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና የተለየ መሆኑን ተናግረዋል ።

ለዚህ እንደምክንያት ያቀረቡት ስልጠናው በስራ ላይ ያሉ ኢንተርፕራይዞች ፍላጎትና ያዘጋጁት መሆኑን ገልጸዋል።

ስልጠናው በክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮና ከልማት ባንክ ጋር በቅንጅት መዘጋጀቱንም አቶ አስፋው ተናግረዋል።

የበለጸጉ ሀገራት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የግዙፍ ኢኮኖሚ ማመኝጫ አድርገው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል ።

አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ባደጉት ሀገራት 50 በመቶ የስራ ዕድል የሚያሠነጩ ስለመሆናቸውም አቶ አስፋው ተናግረዋል።

አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የኑሮ ውድነትን፣ የዋጋ መናርንና ስራ አጥነትን ሀሰተኛ የውጭ ምንዛሬ ዕጥረቶችን ለመቀነስም አይነተኛ ሚና ይጫወታሉ ሲሉ ተናግረዋል ።

በክልሉ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም ልማት ባንኩ ጠንቅቆ ያውቀዋል ያሉት አቶ አስፋው የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ባንኩ ጠንቅቆ ይሰራልም ብለዋል።

ባንኩ በቦንጋ ዲስትሪክት፣በሚዛን አማን፣በቴፒና በቅርቡም በዳውሮ ታርጫ ቅርንጫፍ በመክፈት ተደራሽነቱን ለማስፋት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል።

ልማት ባንኩ ከክልሉ መንግስት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ከ600 ሚሊዮን በላይ የገንዘብ መጠን ያላቸውን ፕሮጀክት ብድርና የሊዝ ፋይናንስ ጥያቄ ተቀብሎ እያስተናገደ ይገኛል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የኢኮኖሚና መሠረተ ልማት አማካሪ ዶክተር ምትኩ በድሩ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በክልሉ ተደራሽነቱን በማስፋት እየሰጠ ያለው አገልግሎት የሚመሰገን ነውም ብለዋል።

በክልሉ 737 ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን የተናገሩት ዶክተር ምትኩ 602 የሚሆኑት በአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ መሠማራታቸውንና 135ቱ በመካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው።

ኢንተርፕራይዞች በክልሉ በብረታብረት፣ ጨርቃጨርቅ፣ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም ኬሚካልና የግንባታ ዕቃዎች በማምረት መስክ ተሰማርተዋል ብለዋል።

በክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት ለአምራች ኢንዱስትሪው በግብኣትነት በመጠቀም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት መጨመር ከግብርና መሪ ወደ ኢንዱስትሪ መሪ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር የምናደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን ነው ብለዋል።

ሂደቱም በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ፋይናንሲንግ ሲታገዝ ልማትን ለማረጋገጥ የምንሄድበትን ርቀት በእጅጉ እንደሚያሳጥር ዶክተር ኢንጂነር ምትኩ ተናግረዋል ።

የሚሰጠው ስልጠና የስራችሁና የህይወታችሁ ወሳኝ ምዕራፍ በመሆኑ በጥብቅ ድሲፒሊን እንድትከታተሉ እጠይቃለሁ ብለዋል።

የክልሉ ኢንዱስተሪና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛው ጋግያብ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችን መካከለኛ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል።

ባለሀብቶቻችን ለክልላችን ጸጋዎቻችን ናቸው ያሉት አቶ ግዛው ጋግያብ ስልጠናውን በተገቢው በመውሰድ ወደ ውጤት ሊቀይሩ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀገራዊ ግብን ለማሳካት ግንባር ቀደም ሆኖ እያገለገለ የሚገኝ ባንክ ነው ብለዋል አቶ ግዛው ።

ከዛሬ ጀምሮ በቦንጋ ከተማ ለ5 ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው ከ600 በላይ ኢንተርፕራይዞች እንደሚሳተፉ ታውቋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *