





የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በምዕራብ ኦሞ ዞን በመኤኒት ሻሻና በመኤኒት ጎልድያ ወረዳ በክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ በቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት(LLRP) የተሰሩ የልማት ሥራችን ጎብኝተዋል፡፡
ስትሪንግ ኮሚቴው በምዕራብ ኦሞ ዞን ሜኒት ሻሻ ወረዳ ይሪኒ ቀበሌ ከይሪኒ ወንዝ በሶላር ሀይል ሰጭነት በተጠለፈ መስኖ የሚለማ የእንስሳት መኖ ልማት የጎበኘ ሲሆን በጣቢያዉም በአንድ ሄክታር መሬት ላይ በመሰኖ የሚለማ የበጋ ስንዴ ልማት ለሰርቶ ማሳያነት፣ በ68 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ ያለዉና 100 ሄክታር ሊያለማ የሚችል የኪሉ መስኖ ልማት ጉብኝት አድርጓል፡፡
የቡክቱ የመኖ ባንክ የተጎበኘ ሲሆን በዉስጡ በ7 ሄክታር መሬት ላይ በሰርቶ ማሳያነት እየለሙ ያሉ የእንስሳት መኖ ልማትን ፣ ካሳባን ፣ስኳር ድንችን ፣በመስኖ የሚለማ የበጋ ስንዴን ፣ዘመናዊ የንብ ቀፎን ፣ጎደረን እና ሙዝ ልማቶችን የጎበኘው፡፡
በተጨማሪም በቢሮ የሚመራው የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በምዕራብ ኦሞ ዞን መኤኒት ጎልዲያ ወረዳ በጫት ቀበሌ 1ኛ ደረጀ ትምህርት ቤት እና በቢያጌሌች ቀበሌዎች ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የወጣቶች እና የሴቶች የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ የእህል ወፍጮ፣ ከባቹማ ከተማ እስከ ጨበራ እየተሰራ ያለው 18 ኪሎ ሜትር መንገድ፣ የዳል ድልድይ ሥራ በመጎብኘት ጊዜያዊ ሥራ ርክክብ በመፈጸም ተዟዙረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳይ ቢሮ እና በሥሩ ያሉ አጋር ድርጅቶች የአርብቶ አደሩንና የከፊል አርሶ አደሮችን ኑሮ ለማሻሻልና በማህበረሰቡ ህይወት ላይ ለውጥ እንዲመጣ ለማስቻል በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛሉ ብለዋል::
በተለይም በክልላችን ቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በሶስት ወረዳዎች በሱርማ፣ በመኤኒት ጎልድያ እና በመኤኒት ሻሻ ወረዳ ከ2013 ዓመት ጀምሮ ዘላቂ በመሬት አያያዝ እና በአርብቶ አደር ኑሮ ማሻሻል ላይ በርካታ ዘርፍ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ግብርና ቢሮን እየደገፈ ይገኛል ብለዋል፡፡
ቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት(LLRP) ከክልሉ መንግሥት በጀት አቅም በላይ የሆኑ በርካታ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን እያከናወነ ነው ያሉት አቶ ማስረሻ በተገቢው መደገፍ እና መከታተል ላይ ትኩራት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ገልጸዋል ፡፡
በክልሉ የአርብቶ አደሩን ህይወት የሚቀይሩ ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቷቸዉ እየተከናወኑ እንደሆነ አቶ ማስረሻ ገልጸዋል
በቀጣይ በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ተግባራት ለማህረሰቡ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ክትትል ማድረግና ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥበቃ እና የተሰሩ ስራዎች በሚዲያ እንዲታጀብ ማድረግ ያስፈልገል ብለዋል፡፡
የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ ቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በሁለቱ ወረዳዎች ዘላቂ በመሬት አያያዝ እና ኑሮ ማሻሻል ላይ በርካታ ውጤታማ ተግባር እያከናወነ መሆኑን በጉብኝቱ መመልከታቸውን ተናግረው በቀጣይ በማሰፋት ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡
አቶ ፀጋዬ ማሞ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት በዞኑ በአርብቶ አደርና ቆላማ አከባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት እየተተገበሩ ያሉ የመሠረተ ልማት አውታሮች የአርብቶ አደሩን ህይወት በተጨባጭ እየለወጠ መሆኑን ገልፀዋል።
በመስክ ምልከታዉ የቢሮ ሀላፊ አቶ ታምሩ ቦኒ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆኑን ገልጸው አሁን የታየው ጠንካራ ሥራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው እንዴ ቢሮ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል እናደርጋለን ብለዋል።
በመስክ ምልከታዉ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጸጋዬ ማሞ ጨምሮ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ፣ የክልሉ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ፣ የክልሉ ስትሪንግ ኮሚቴ፣ የዞንና የወረዳው አመራር፣ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና የፕሮጀክቱ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተገኝቷል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
