በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የተመራው ልዑክ ቦንጋ ከተማ ገባ።

Spread the love

ልዑኩ በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ጎጀብ ከተማ ሲደርስ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የካፋ ዞን ከፍተኛ አመራሮችና የአካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ልዑካኑ በቆይታው የፈረንሳይ ፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ሰነ-ስርዓት በቦንጋ ከተማ በማካሄድ ለሲዳማ ብሄራዊ ክልል ርክክብ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

በቦንጋ ከተማ ዛሬ ከሰዓት የፓናል ውይይት የሚካሄድ ሲሆን ነገ ጠዋት በአደባባይ ላይ በተለያዩ ትርኢቶች ለታዳሚዎች ቀርቦ የችቦ ማብራትና የሽኝት መርሃ-ግብር እንደሚከናወን ይጠበቃል።

”ኢትዮጵያ ትወዳዳራለች፣ ተወዳድራም ታሸንፉ” በሚል መሪ ሀሳብ የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የችቦ ማብራት ንቅናቄ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ተጀምሮ በአራት ክልሎች መካሄዱ የሚታወስ ነው።

መርሃ-ግብሩ በእግር ጉዞ የተጀመረ ሲሆን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ችባውን በቦንጋ ከተማ በማብራት ለቀጣይ ተረኛው የሲዳማ ክልል እንደሚያስረክብም ተገልጿል።

ለእንግዶቹ የእንኳን መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ መርሃግብሩ ክልሉን ገጽታ በጉልህ የሚገነባ እንደሆነ ተናግረዋል።

በልዑካን ቡድኑ ውስጥ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚዎች፣የ2024 ፓርስ ኦሎምፒክ ቴክንክ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

በቦንጋ ከተማ በሚኖረው መርሀግብር የተለያዩ ስፖርታዊ ትርዒቶች እንደሚቀርብም ከወጣው መርሀግብር ተመላክቷል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *