
ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት አስመልክቶ በዲጂታል ሚዲያው ላይ እየተሰራጩ ያሉ ሀሰተኛ መረጃዎችን ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የኢፌዲሪ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አሳስቧል፡፡
አካባቢያዊ፣ ክልላዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ይፋዊ ግንኙነቶች በጽህፈት ቤቱ ይፋዊ የዲጂታል አማራጮች ብቻ እንደሚሰራጩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የፅህፈት ቤቱን ሎጎ አላግባብ በመጠቀም የውሸት መረጃዎችን ከሚያሰራጩ አካላት ማህበረሰቡ እራሱን እንዲጠብቅም አሳስቧል፡፡
