


ምክርቤቱ በዛሬው ውሎ የምክርቤቱ አባላት የአሰራርና የአባላት ሥነሥርዓት ለመደንገግ በወጣ ደንብ ላይ መክሯል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የብሔረሰቦች ምክርቤት የአሰራርና የአባላት ሥነሥርዓት ለመደንገግ የወጣ ደንብ በአቶ መቱ አኩ ቀርቧል።
የክልሉን ብሔረሰቦች ምክርቤት ሥልጣን እና ተግባርን ለመዘርዘር በወጣው አዋጅ ቁጥር 10/2014 አንቀጽ 43 መሠረት በማድረግ ደንቡ መዘጋጀቱን አቶ መቱ አኩ ገልጸዋል ።
የተዘጋጀው ደንብ የብሔረሰቦች ምክርቤት በክልሉ ህገመንግስት የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር እንዲሁም ሌሎች ተግባራትን በኃላፊነት እንዲወጣ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ደንቡ ተዘጋጅቷል ብለዋል።
ለውይይት የቀረበው የክልሉ ብሔረሰቦች ምክርቤት የአሰራርና የአባላት ሥነሥርዓት ለመደንገግ የወጣው ደንብ በአስራ ስድስት ክፍሎች እና በ98 አንቀጾች የተዘጋጀ ነው።
የምክርቤቱ አባላት ሀገራችን በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሀገሪቱ በግልጽ የታወቁትን የሥነምግባር መርሆዎችን ከክልሉ ነባራዊ ሁኔታና ከስራው ጋር አጣጥሞ በተግባር ላይ ማዋል እንደሚገባ በደንቡ አንቀጽ 48 ላይ ተደንግጓል ።
ተዘጋጅቶ በቀረበው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የብሔረሰቦች ምክርቤት ለመደንገግ የአሰራርና የአባላት ሥነሥርዓት ለመደንገግ በወጣ ደንብ ላይ የምክርቤቱ አባላት ከተወያዩ በኋላ ስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል ።
የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ ጉባኤው የተሳካ አባለትም ለብሔረሰቦች ምክር ቤት መጠናከር የተሻለ ግብኣት የሰጡበት መሆኑ እንዳስደሰታቸው በመግለፅ ለጉባኤው ስኬትና በሰላም መጠናቀቅ ድርሻ ያላቸውን አካላት ሁሉ አመስግነዋል።
