


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በሁለተኛ ቀን ውሎው በክልሉ መንግሥት የቀረቡ 11 ረቂቅ አዋጆችንና 1 ደንብ መርምሮ አፅድቀዋል።
የረቂቅ አዋጆቹ ዓላማና አስፈላጊነትና እንዲሁም ዝርዝር ይዘት እና የተፈጻሚነት ወሰን ላይ በምክር ቤቱ ዋና አፌጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በዝርዝር ተተችተው ለምክር ቤቱ ውሳኔ የቀረቡ ረቂቅ አዋጆች የክልሉን ሁለንተናዊ ዕድገት በማፋጠን የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጎላ ድርሻ እንዳላቸው የተመላከተ ሲሆን በቀረበው ረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ሀሳብ አስተያየት ተነስቷል።
ለአዋጁ ተግባራዊነት የሁሉም ባለድርሻ አካል ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁት የምክር ቤቱ አባላት የማስፈፀሚያ ደንቦችና መመሪያዎች ተዘጋጅተው ወደ ተግባር ተገብተው ተገቢውን አግልግሎት እንዲሰጥ ትኩረት መደረግ እንዳለበትም ነው የገለጹት።
በረቂቅ አዋጆቹ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረቡት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በአዋጆቹ ላይ የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በጥልቀት የገመገመ መሆኑን ገልጸዋል።
አዋጆቸም፦
1.የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ስልጣንና ተግባር እንደገና ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
2.የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ
3.በክልሉ የቀበሌ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ተግባር ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
4.የክልሉ መንግሥት አስተዳደር ስነስርዓት ለመደንገግ የወጣ አዋጅ፣
5.የክልሉ መንግሥት የባህል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም እና እውቅና ለመስጠት የወጣ አዋጅ፣
6.የከተማ ውሃ ፈሳሽ አግልግሎት ድርጅት ማቋቋም ረቂቅ አዋጅ፣
7.የመስኖ ውሃ ተጠቃሚ ማህበራትን ለማስተዳደር የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
8.የክልሉ ምክር ቤት ጽ/ቤት ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
9.የክልሉ የታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ፣
10.የክልሉ መንግሥት የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ፣
11.የክልሉ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን አደረጃጀት፡ ሥልጠንና ተግባር ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅ
12.የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሠራተኞች ደንብ በምክር ቤቱ አባላት ሙሉ ድምጽ ፀድቋል።
በዕድገቱ በዛብህ
