ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የኢትዮጵያን ምርት የመግዛት ባህል ማዳበር ያሰፈልጋል፦ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

Spread the love

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የኢትዮጵያን ምርት የመግዛት ባህል ማዳበር ይገባል ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር “የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሀሳብ ካዘጋጀው የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን ትኩረቱን የጥራት መሰረተ ልማት ላይ ያደረገ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት፤ ጥራት ለምርቶች ሁሉ መሰረት ሊሆን ይገባል።

የሀገር ውስጥ ምርት ጥራት የለውም ከሚል ብሂል በመውጣት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ኢትዮጵያ ውስጥ ጥራት ያላው ምርትና አገልግሎት መስጠት ይቻላል የሚል ባህልን ማዳበር ይገባል።

ኢትዮጵያ በምርት ዓይነቶች እምቅ አቅም ያላት መሆኗን ገልጸው፤ የኢትዮጵያን ምርቶች የመግዛትና የመጠቀም ልምምድ ማሳደግ አለብን ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሚገኙ አምራቾች ምርትን በጥራት በማምረት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *