




የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ዞኑ በተፈጥሮ ሀብቱ የበለፀገ በተለይም በተፈጥሮ ደን፣ በቱሪስት መስህቦች፣ ቡናና ቅመማ ቅመም፣ በማርና በሻይ ምርት የሚታወቅና ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ብሎም ኤክስፖርት በማድረግ ከአካባቢው አልፎ ለሀገር አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም ዞኑ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በጋራ ተፈቃቅረው የሚኖሩባት ሠላማዊና የህብረብሔራዊነት ተምሳሌት መሆኗን ገልፀው ሰልጣኞች በስልጠና ወቅት ሠላማዊና ደስተኛ ሆነው እንዲሰለጥኑና ከስልጠና በኋላ ዞኑን እንዲያስተዋዉቁ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እንደሻው በመክፈቻ ንግግራቸው ስልጠናው ” ብቃት ለቴክኒኪና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመሳሳይ ሁኔታ የዘርፉን አዳዲስ እሳቤዎች ለማስተግበር ያስችል ዘንድ እየተሰጠ ያለዉን ሥልጠና በአግባቡ ተከታትለዉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል ።
የቴክንክና ሙያ ተቋማት ለሀገር ብቁ የሰለጠነ የሰዉ ሀይል በማቅረብ በኩል የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንዳለ አክለዋል።
በፌደራል ሥራና ክህሎት ሚንስቴር የግብርናና ሥርዓተ ትምህርት ሥልጠና ደስክ ሀላፊ አቶ ሚልዮን ቡሎ ሥልጠናዉ የዘርፉን አዳዲስ እሳቤዎችና የሰልጣኞች ምና ፣አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ መሠረታዊ ይዘቶች፣ሥራ ፈጠራ በቴክንክና ሙያ ሥርዓት ፣ ሰዉ ተኮር ክህሎት፣ የማስተማር ሥነ ዘዴና የሥልጠና ጥራት በቴክንክና ሙያ ተቋማት ምን መልክ ይኖረዋል በሚል ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ብለዋል።
ሥልጠናዉን በተገቢዉ በመከታተል ለሀገር ተገቢዉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሄም ዳንኤል ለሰልጣኞቹ የእንኳን ደህና መጣችሁና ስልጠናዉን በአግባቡ ተከታትለው ዕውቀት እንዲጨብጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ስልጠናዉ ለተከታታይ 12 ቀናት አንደሚቆይም ተገልጿል ያለው የሸካ ዞን ኮሙኒኬሽን ነው።
